የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ማህበር በአ/ው/ወ/ከ/ል/ቤ/ጽ/ቤት ስር ተደራጅቶ የሚንቀሳቀስ የእንጨትና ብረታ ብረት ማህበር ሲሆን በወረዳው በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው እራሳቸውን ወደ ተሻለ የስኬት ጉዞ እያመሩ ካሉት ኢንተርፕራይዞች አንዱ ነው፡፡ ይህ ኢንተርፕራይዝ የተቋቋመው ከአከባቢው በተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በወረዳው ላይ ካሉት የመኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ማህበራት የተሻለ እንቅስቃሴ የሚያደርግና ከጊዜ ወደ ግዜ አቅሙን እያሳደገ የመጣ ሞዴል ማህበር ነው፡፡ ስለሆነም የዚህ ውጤታማ ማህበር አጠቃላይ ከመነሻ ጀምሮ እስከ አሁን ያለውን የውጤታማነት ጉዞና ተሞክሮ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ማህበር የተመሰረተው በአ/ው/ወ/ከ/ል/ቤ/ጽ/ቤት ስር በ2010 ዓ/ም ሲሆን ከአከባቢው በተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች ነው፡፡ የማህበሩ አባላት ወ፡07, ሴ፡--, ድ፡07 ስሆኑ እነዚህ ወጣቶች መነሻ ካፒታል ቅድመ ብድር ቁጠባ 20,000 ብር በማህበሩ አባላት በማዋጣት ከአበዳሪ ድርጂት /ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም 200,000 ብር ብድር በመበደር የእንጨትና ብረታ ብረት ስራን በመጀመር ለራሳቸው ስራ ፈጣሪ ለመሆን እና ከጥገኝነት በመላቀቅ ብሎም ለሌሎች ስራ ለመፍጠር በነበራቸው ተነሳሽነት ይህንን ማህበር መፍጠር ችለዋል፡፡ የማህበሩንም ስም አፍራን በማለት የሰየሙት ሲሆን ትርጉሙም ደስታ እንደለማለት ነው፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ማህበር ሀላፊነታቸውን ጠንቅቀው በሚያውቁና ለማህበሩ እድገትና ለውጥ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው በሚንቀሳቀሱ ንቁ ወጣቶች የተመሰረተ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡ ኢተርፕራይዝ የተለያዩ የአመራር አካላት ማለትም ሊቀመንበር፣ፀሀፊና ገንዘብ ያዥ ያሉት ሲሆን ሁሉም አካላት የኢንተርፕራይዝን ተቋማዊ አደረጃጀት ውጤታማ ለማድረግ እንደየድርሻቸው ጠንክረው የሚሰሩ ናቸው፡፡
ቀደም ሲል እንደተገለፀው የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ማህበር የተመሰረተው ከቀበሌው ዉስጥ የተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች ነው፡፡ አነዚህ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችን በማምረት ለተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑት ተቋማት እና ድርጅቶች እንድውም ግለሰቦች ጋር በመሆን የተለያዩ አማራጮችን በመመልከት የጀመሩ ስሆን ሀሳባቸውን የጋራ አድርገው በመወያየት በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅት እራሳቸውን ከስራ አጥነትና ከጥገኝነት በማላቀቅ ከዚህም አልፈው ለሌሎች የሥራ እድል መፍጠር
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው ወደ ስራ ከገባ በኋላ ገበያው ላይ ካሉ ተወዳዳሪዎቹ ልቆ ለመገኘት የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎችን ነድፎ በመንቀሳቀስ የውጤታማነት ጎዞ ላይ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ከሌሎች በተመሳሳይ ዘርፍ ከተሰማሩት ኢንተርፕራይዞች በተነፃፃሪ በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችን አምርተው ለማቅረብ የራሱን የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎች ይጠቀማል፡፡ እንዲሁም የተሰጣቸውን ስራ ከተቀመጠለት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ትርፋማነታቸውን መጨመር ችለዋል፡፡
ከዋጋ አንፃር
የእንጨትና ብረታ በረት ምርት የገበያ ዋጋን ለመወዳደር ከሌሎች ማህበራት ጋር በመፎካከር ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለተገልጋዩ በማቅረብ ውጤታማ መሆን ይቻላል፡፡
ከጥራት አንፃር
የዋጋ ነገር ሲነሳ ጥራት አብሮ መነሳቱ የግድ ነው በማንኛውም የቢዝነስ ዘርፍ እነዚህ ሁለት ነገሮች ተያይዘው መነሳታቸው የተለመደ ነገር በመሆኑ ጥራት ያለውና እስታንዳርዱን የጠበቀ ብሎኬት ከሚጠይቀው አቅምና ጊዜ አንፃር ዋጋው ከፍ ማለቱ አይቀርም ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በጥራቱ የወረደና እስታንዳርዱን ያልጠበቀ ብሎኬት ዋጋው ሊቀንስ ይችላል፡፡
ገበያው የሚፈልገውን የምርት ጥራትና ስታንዳርድ እንዴት ሊጠብቅ ቻለ
በእንጨትና ብረታ ብረት ስራ አለም ላይ ጥራትና እስታንዳርድ የተለያዩ ነገሮች ብሆኑም አንዳቸውም ከአንዳቸው በተያያዘው አቅሞች ሊረጋገጡ ይችላሉ፡፡ በቂ እውቀት፣ልምድ ገንዘብና ትኩረት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
የአከባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ለማጥናት በራሳቸው መንገድ በመንቀሳቀስ ከተለያዩ አካላት ልምድ የቀሰሙ ሲሆን ያለባቸውን የክህሎት ጋፕ ለመድፈን መንግስት (ወረዳው) በሚያመቻችላቸው አጫጭር ስልጠና በመሳተፍ እውቀታቸውን ያዳበሩ ሲሆን ዘርፉ የሚጠይቀውን ጥራትና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ ብሎም ገበያው ውስጥ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቆየት ያላቸውን እውቀት እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችን በማዘጋጀት ከተለያዩ በዘርፉ ከተሰማሩ አካላት ተሞክሮና ልምድ በመቅሰም በዘርፉ ጥሩ ልምድ ያካበተ ሲሆን ስራው ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ በማመንጨት ልምድ ማካበታቸው ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ማህበሩ ከመነሻ ጀምሮ የነበረባቸውን የልምድ ማነስ በማሻሻል ክፍተቶቻቸውን ከማሟላታቸውም በላይ ጥራትና እስታንዳርዱን የጠበቀ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችን በማምረት ጥሩ ልምድ መቅሰም ችለዋል፡፡
1.የማህበሩ አመሰራረት
2.የኢንተርፕራይዙ ተቋሚው ስራ አመራርና አደረጃጀት
3.የኢንተርፕራይዙ ልማታዊ አስተሳሰብና የስኬታማነት ጉዞ
3.1 የኢንተርፕራይዙ ልማታዊ አስተሳሰብና የስኬታማነት ጉዞ
3.2 የሥራ ክህሎት አጠቃቀም
3.3 በገበያ ውስጥ በምርት ጥራትና በዋጋ እንዴት ተወዳዳሪ መሆን ቻሉ
የኢንተርፕራይዙ የምርት ጥራትን እስታንዳርድ ከበቂ እውቀት
የኢንተርፕራይዙ የምርት ጥራትን እስታንዳርድ ከልምድ አኳያ
በዚህ ዘርፍ የተሰማራ የትኛውም አካል ገንዘብ ሳይዝ ከተፎካካሪዎቹ እኩል ይራመዳል ብሎ ማሰብ በጣም ይከብዳል፡፡ በእርግጥ የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረት ስራን ለመስራት 200,000 ብር የመነሻ ካፒታል ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በመመደር ወደ ተግባር የገቡ በመሆኑ ስራውን በጥራት ለመስራት ያደርጋል፡፡
ይህ ኢንተርፕራይዝ ለደረሰበት የስኬት ጎዳና ቁልፍ ሚና የሚጫወተው ቁጠባ መሆኑን በመገንዘብ እና የባለሙያ የድጋፍ አገልግሎት በተገቢው በመረዳት የቁጠባ ባህልን ከአመለካከትም ሆነ በተግባር አየቆጠቡ የካፒታል መጠናቸውን ከማሳደግ አንጻር ባቀዱት መሰረት እየቆጠቡ መሆናቸውን የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም የቁጠባ ደብተራቸው ያመላክታል፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ማህበር መንግስት ያመቻቸላቸውን እድል በመጠቀም ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ 200,000 ብር በመበደር እንደ መነሻ ካፒታል በመጠቀም እና የማምረቻና መሸጫ ቦታ (ሼድ) ተመቻችተውላቸው ወደ ሰራ የተሰማሩና ውጤታማ መሆናቸውን እና በአሁኑ ወክት የካፒታል መጠናቸው እያደገ መምጣቱን የኦድት መረጃቸው ያሳያል፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውቴቶች ማምረት ማህበር ተቋማዊ የአመራርነትና አደረጃጀት ውጤታማነት ስንመለከት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቀስቃሽና ጎትጓች ሳያስፈልጋቸው ሀላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ናቸው፡፡ የማህበሩ ተቋማዊ የአመራርና አደረጃጀት በሶስት ሚናዎች ተከፈለ ሲሆን እነሱም፡- ፀሀፊ፣ሊቀመንበርና፣ገንዘብ ያዥ ናቸው፡፡ ከፀሀፊው ሚና ስንነሳ አጠቃላይ በማህበሩ የሚከወኑ ከፁሁፍ ጋር በተያያዘ የሚከወኑ ጉዳዮችን የሚፈፅም ሲሆን ከሂሳብ መዝገብ የተያያዙ ስራዎችንም ያከናውናል፡፡ ሌላው ገንዘብ ያዥ ሲሆን አጠቃላይ በማህበሩ የሚንቀሳቀሱ ሂሳቦችን በኃላፊነት ያንቀሳቅሳል፡፡ ገንዘብ በማህበሩ ስም ወጪ ሲደረግም ሆነ ገቢ ሲደረግ አጠቃላይ የሚከናወኑት በገንዘብ ያዡ በኩል ነው፡፡ ሶስተኛው አመራር ሊቀመንበሩ ወይንም ሰብሳቢ ሲሆን እንደ አጠቃላይ ለማህበሩ ተጠሪ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ይህ አመራር በአብዛኛው ተንቀሳቃሽ ሲሆን ማህበሩን በሚመከለት ጉዳዮችን ለማስፈፀም ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚጓዝበት ሁኔታ አለ፡፡ በተለይ የገበያ ትስስር ሲፈጠር እንዲሁም ማህበሩ የሚሳተፍባቸው መድረኮች ካሉ ማህበሩን ወክሎ በመሄድ ጉዳዮችን ያስፈፅማል፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ማህበር ወደ ስራ የገባው በ200,000 ብር መነሻ ካፒታል ነው፡፡ ማህበሩ የተመሰረተው ከአከባቢው በተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች እንደመሆናቸው መጠን ለስራ ማስኬጃ 200,000 ብር በአግባቡ በመጠቀም እንዲሁም ከሚያገኙት ትርፍ አብዛኛውን በመቆጠብ አሁን ላይ ጥሩ ካፒታል ያለው ማህበር መሆን ችሏል፡፡
የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረት ማህበር የተመሰረተው ከአከባቢው በተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች ስሆን እራሳቸውን ከስራ አጥነትና ከጥገኝነት አላቀው አፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረት በሚባለው ማህበራቸው ስር ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ችለዋል፡፡

የአፍራን እንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረት ማህበር በብዙ መለኪያዎች ለሌሎች በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው በተለይ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረት ላይ ለሚሰሩ ማህበራት ምሳሌና የምርት ምርጥ ተሞክሮ መማሪያ መሆን እንደሚችል ማየት ችለናል፡፡ በመሆኑም ሌሎች ማህበራት የዚህን ውጤታማ ማህበር አካሄድና ተሞክሮ ወደ ራሳቸው የሚመጡበትና የዚህን ኢንተርፕራይዝ ፈለግ በመከተል ቀጣይ ለሚመጡ ማህበራት ሞዴል የሚሆንበት እድል ሰፊ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved