የአልቾ ውሪሮ ህዝብ የሚጠቀማቸው ባህላዊ መድኃኒቶች

ተ.ቁ ስም ዝርዝር አገልግሎታቸው
1) ሹንፍ(ፌጦ) ለምች፣ለራስ ምታት፤ለጨጓራና ወዘተ…
2) ቱመ(ነጭ ሽንኩርት) ለጉንፋን፣ለብርድና ወዘተ…
3) ቆበሪቾ ለሴጣን፣ጂኒ ቤት እንዳይደርስ ለማድረግ፣ለምች ወዘተ…
4) መዛ ቁጠል ለቁስል፣ወዘተ…
5) አንጩሌ ቡጉንጅ ከወጣብን በእሳት ቅጠሉን በማሞቅ ቡጉንጁ የወጣበት ቦታ ለይ መያዝ ቡጉንጅን ይፈዉሳል
6) ስጋ ጥብስ(በሰር ጥብስ) ለደም ብዛት፣ለደም ግፊት፣ወዘተ…
7) ዳማከሴ ለምች፣ለጉንፋን፣ወዘተ…
8) አናምሮ ለጨጓራ፣ለሆድ ህመም፣ወዘተ…
9) ሬት(ዮራብ ቀርሼ) ለፎረፎር፣ወዘተ…
10) ኮሶ(ሴጦ) ለኮሶ በሽታ ሁነኛ መድሀኒት ነው
11) ሲኖ ዌሴ የተሰበረ ሰውን ሰውነት ለማከም፣ወዘተ…
12) ሹማረት ዌሴ ከብቶች ሲወልዱ የእንግዴ ልጅ አሎጣም ካለ ይህን የእንሰት አይነት በልተው እንዲወጣ ማድረግ ይቻላል
13) ቅቢናር ዌሴ የተሰበረ ሰውነትን ለመጠገን ይሆናል
14) አይዋኜ ዌሴ ቡጉንጅን ለማምገል ያገለግላል
15) ጋራዬ ዌሴ ሰውነት ለማጠንከር ያገለግላል
16) ደም ዋረድ ዌሴ ሽንት እንቢ ያለው ሰው እነዲወጣለት ማድረግ የሚችል የእንሰት አይነት ነው
17) ተልባ ለጨጓራ አሪፍ መድሀኒት ነው
18) ኢሴቼ ለጥርስ ህመም ፍቱን መድሀኒት ነው
19) አናምሮ ለምች
20) ዶቦቆ ለቁርጠት
21) ይሶክ ስር ለምች፣ለእርግዝና መከላከያ ያገለግላል
22) ጪንብለቤ ለጨጓራ፣ለሆድ መነፋት መድኃኒት ነው
23) ፈንፈ ለጋኛ አማረይ ቤንዘይ የሰኩያን፡፡
24) ነትራር ከቅቤ አንድ ላይ በማድረግ በአፍነጫ ከተወሰደ ለራስ ምታት ሁነኛ መድኃኒት ነው
25) ጩቁኜ ለልክፍት
26) ጂንጅቤል ለጉንፋን
27) የጠይ በደር ለሴት ልጅ የወር አበባ በመጣ ጊዜ ያለውን ቁርጠት ያስታግሳል

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved