በዝርዝር

የጣንዤ ትክል ድንጋዮች

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ታሪካዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ በጣንዤ ቀበሌ ስማኤል መንደር ውስጥ

በዝርዝር

ትክል ድንጋዮች የሚገኙት ከወረዳዋ ርዕሰ ከተማ ቃዋቆቶ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 8 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በጣንዤ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ልዩ ስሙ ስማኤል በሚባለው መንደር የሚገኙ ሲሆን ከጣንዤ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በስተ ደቡብ አቅጣጫ በ0.5 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ትክል ድንጋዮቹ በአንድ ቦታ የተተከሉና ረጅም እድሜ እንዳላቸው ያያቸው ሁሉ ይመሰክራል፡፡ ብዛታቸው ሁለት ሆኖ በሞላላ ቅርፅ ተሰርተው የበለጠ ልዩና ተደናቂ የሚያደርጋቸው ጡት መሰል ነገር ያላቸው መሆኑን በጎድን አጥንት መልክ የተጫሩ ጭረቶቹም ለምን ታስበው እንደተቀረፁ የሚያመራምርና የሚያጠያይቅ መሆኑ ነው፡፡

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved