የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ታሪካዊ
የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ዉሾ ቀበሌ
በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው በወይራ ወንዝ ላይከአንድ ትልቅ የሃገር በቀል ዛፍ የተሰራ ሆኖ ከስልጤ እናቶች አንዷ በሆኑት አጃማት መኩላ አማካኝት የተጣለ እንደሆነና እድሜውም 600 ዓመት በላይ ያስቆጠረ መሆኑ ይገለፃል፡፡ እስከ አሁን ለአገልግሎት መዋሉና የጊዜ እርዝመቱን ስንመለከት በጣም የሚያስገርም ከመሆኑም በላይ ለጥናትና ምርምር የሚፈልጉ የሃገርና የውጭ ቱሪስቶች ጥሩ አጋጣሚ የሚፈጥርላቸዉ መስህብ ነው፡፡ ይህ እድሜ ጠገብ እንጨት በጣም አስገራሚ የሆነ ታሪካዊ ክስተት እንደሆነ የማያጠራጥር ሆኖ ቢያንስ ለ9 ትውልዶች አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል ማለት ይቻላል፡፡ እንጨቷ አንድ ወጥ ሆኖ ሰፋ ያለችና መሀል አካባቢ ጉርጉድ ብላ ትገኛለች፡፡ ወገር ዘራማ ከቃወቀቆቶ ከተማ በ16 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በስተሰሜን አቅጣጫ ትገኛለች፡፡በመስህቡ ዙሪያ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦችን በቀላሉ በአንድ ጀምበር በቅርብ እርቀት ማየት ይቻላል፡፡ሃገርንማወቅ ከአካባቢ ይጀምረል እንላለን!
© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved
By logging in you agree to our Terms and Conditions and Privacy Policy