የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ታሪካዊ
የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ አገታ ቀበሌ
የአብናዝ ጎሽቶ መስጅድ በአፄ ሚኒሊክ ዘመነ መንግስት በአብድናዝ ጎሽቶ በራሳቸው እንደተሰራ የአካባቢው ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ መስጅዱ በአገታ ቀበሌ ምንም መስጅድ በሌለበት ወቅት የተሰራ የመጀመሪያ መስጅድ ነው፡፡ አብድናዝ ጎሽቶ የመስጅዱ መስራች የአካባቢው ታዋቂ ህመም እንደነበሩም ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡ ከአብናዝ ጎሽቶ የሃይማኖት ትምህርት ለመማር በየቦታው ይመጡ እንደነበረ የአካባቢው ሽማግሌዎች ያወጋሉ፡፡ መስጅዱ መጀመሪያ ሲሰራ የሳር ክዳን ሆኖ ቢያንስ 3-4 ጊዜ ተቀይሮ አሁንም ክዳኑ በሳር ሆኖ ነው የሚገኘው፡፡ አብድናዝ ጎሽቶ ከሃይማኖታዊ ትምሀርት ተጨማሪ ጥበባዊ ትምህርትም እንዳስተማሩ ይታወቃል፡፡ የአብድናዝ መስጅድ በሰፊ ቦታ እንደተመሠረተ ነበር ነገር ግን ቦታው እየቀነሰ መቶ ቢያንስ 1 ሄ/ር ቦታ ላይ ይገኛል ግቢውም በሩቅ ሆኖ ሲያዩት የተለያየ ዛፎች ተጠጋግተው ስለሚገኙበት ከፓርክ ተመሳሳይ ይዘት አለው፡፡ አብድናዝ ጎሽቶ ተወልደው ያደጉት በስልጢ ወረዳ በአስከኮላ አካባቢ ሲሆን በወቅቱ በነበረው የጦርነት ዘመን ወደ ወረዳችን የመጡትን መጠው ኤጃሬ ላይ ሰፈረውና በዛ አካባቢ በርካታ ቤተሰብ መስርተው ኖረዋል፡፡ 1902ዎቹ የተወለዱት አብድናዝ ጎሽቶ በ150 አመታቸው ከአማረ አካባቢ ከመጡ ጦረኞች ‹‹በሰንበት አማረ›› በሚባል በዚህ በሞት ተለይቶዋል፡፡ የገደላቸውን ልጅ በዛ በሩቅ ቦታ ማለትም በጎንደር ልጁ ገና እንድተወለደ እኔን የሚገድለኝ ልጅ አሁን ተወለደ፣ አሁን እረኛ ሆነ፣ አሁን ጎረምሳ ሆነ ወዘተ ---- እያሉ የልጁን የእድገት ሂደት በመንፈስ መከታተላቸው ሌላው አግራሞት ሆነ፡፡ እነሱም ትንቢያ በሰጡት በራሱ መቶ ገደላቸው፡፡ እርሳቸውንም ገድሎ መቆየት አልቻለም፡፡ ልጁም ወዲያውኑ ነበር የተገደለው የአብድናዝ ጎሽቶ አግራሞት ታሪካቸው ደግሞ እሳቸው አይንም ሆነ የአይን ቅርፅ እንዳልነበራቸው ነው በታሪኩ ያወጉን ሽማግሌዎች የነገሩን ግን አቅጣጫዎችን ሚጓዙት የነበረው አይን ካለው ሰው ጋ በማይተናነስ ሁኔታ ነበር፡፡ አብድናዝ ጎሽቶ የአራት ወንድ ልጅና የሶስት ሴት ልጆች አባትም ነበሩ፡፡ ልጆቻቸውም በወረዳው በሚገኙ ወደ ተለያየ ቀበሌያት ይኖራሉ፡፡ ከሰባቱ ልጆቻቸው አንዷን ኡስቤ ሼህ አብድናዝ በመባል የምትታወቀውን በወቅቱ ከዘመቱ የአማራ ጦረኞች ተማርኮ እንደተወለደችናአሁን አማራ ጎንደር አካባቢ ቤተ ዘመዶቹ እንዳሉ ይነገራል፡፡ በመጨረሻም መስጅዱ የ150 ዓመት እድሜ እንዳለውና በወረዳችን ጥንታዊ ከሆኑ ታሪካዊ ቅርሶች አንዱ ነው፡፡ ስለዚህም ለወደፊቱ የበለጠ ታሪኩ ተጠንቶና እንክብካቤ ተደርጎለት ለተፈለገበት ዓላማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ይወጣ እያልን ተሰናበትን፡፡
© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved
By logging in you agree to our Terms and Conditions and Privacy Policy