በዝርዝር

አምስቲ ጊስቲቻ ያፎልቡይ ኤት

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ታሪካዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ቃዋቆቾ 01 ቀበሌ አብራር መስጂድ ግቢ ዉስጥ

በዝርዝር

ለከተማዋ ስያሜ መነሻ የነበረ ክስተትን እንዳስተናገደ የሚነገርለት ስፍራ ቦታቸውን በስልጥኛ አምስቲ ጊስቲቸ ያፎልቡይ ኤት ይሉታል፡፡ አምስቱ ሴት አያቶች ያረፉበት ቦታ ማለት ነው፡፡ በስልጤ ብሔረሰብ በአንድ የታሪክ ወቅት ሀጅ አልዬ በሚባል የሃይማኖት አባት መሪነት ወደ አካባቢው ከመጡ በርካታ ሰዎች ጋር በተያያዘ የመጡ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከነዚህም መካከል ዋናዎቹ ጊስቲ ሙሉካ፣ ጊስቲ ሸምሲያ፣ ጊስቲ መኪያ(መኩላ)፣ ጊስቲ ጣሂራትና ጊስቲ ሁጃራት ናቸው፡፡ እነዚህን ሴቶች ነው እንግዳ ማ/ሰቡ አምስቲ ጊስቲቸ በማለት በአፈ ታሪክ ስማቸውን ያቆያቸው፡፡ ቦታውም እነዚህም ሴቶች ከውጪ መጀመሪያ ሲመጡ ያረፉበት እንደሆነ ይነገራል፡፡ ታዲያ በቦታው ላይ ማረፋቸው ከከተማው ስያሜ ጋር እንዴት ነው የሚገናኘው? ከላይ የተጠቀሱት ሴቶች ረጅም መንገድ ተጉዘው በመምጣታቸው ደካክመዋል፡፡ ቡና አስፈለጋቸው በአካባቢው ከነበሩ ማ/ሰቦች ማግኘት ስላልቻሉ ወደ ፈጣሪያቸው ዞረው ቡና እንዲሰጣቸው መለመን ጀመሩ በመሠረቱም አምስቱ ሴቶችና አብረዋቸው የመጡ በርካታ ሰዎች ከእስልምና ጋር በተያያዘ የመጡ እንደነበር ነገራል፡፡ በመሆኑም ጠንካራ አማኞች በመሆናቸው ፈጣሪ ባረፉበት ቦታ ላይ ቡና እንዳዘነበላቸውና ይህንንም የቡና ክምር ለረጅም ጊዜ ሲጠቀሙ እንደቆዩ ይነገራል፡፡ በስልጥኛ ቋንቋ ቃዋቆቶ ማለት የቡና ተራራ ማለት ነው፡፡ ከላይ በመግቢያችን እንደገለፅነው እኚህ ከላይ ያስተዋወቅናቸው መስህቦች በወረዳችን ከሚገኙ በርካታ ቅርሶች ጥቂቶቹ እንደሆኑ በማሳሰብ ቅርሶችን የማንነት መገለጫዎች ከመሆናቸው በተጨማሪ ለወረዳችንም የገፅታ ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ፋይዳቸው የጎላ ነው፡፡

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved