በዝርዝር

የጊስቲጣሂራት ጥንታዊ መስጂድ

የቱሪስት መስህቡ አይነት፡ : ሐይማኖታዊ

የቱሪስት መስህቡ ያለበት ቦታ፡: በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ አገታ ቀበሌ

በዝርዝር

የጊስቲጣሂራት ጥንታዊ መስጂድ ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ በአሊቾ ውሪሮ በኩል ወደ ወልቂጤ በሚወስደው መንገድ 35ኪ/ሜ ርቀት ላይ በአገታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሶጃት ተብሎ በሚጠራ መንደር ከቃዋቆቶ ደግሞ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ13 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ያገኙታል፡፡ መስጂዱ በጥንት ጊዜ ከምስራቅ አቅጣጫ በመምጣት አካባቢው ላይ ሰፍረው ለዛሬው የስልጤ ብሔረሰብ ጎሳዎች ምንጭ ከሆኑት ታላላቅ ሴት አያቶች መካከል በአንዷ (ጊስት ጣሂራት) አማካይነት እንደተገነባ የሚነገር ሲሆን ከአገታ ተራራ ስር ከሚገኝ አንድ ቋጥኝ ተቦርቡሮ የተሰራ ነው፡፡መስጂዱ ከ500 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት የድንጋይ ፍልፍል መስጂድ ነው፡፡መስጂዱጋ ለመድረስ በሀገር በቀል ቁጥቋጦዎች የተሸፈነዉን የአገታ ተራራ እየተንፋቀቁ በታላቅ ጀግንነትና የጎብኚነት ስሜት መውረድን ይጠይቃል፡፡አድቬንቸርቱር ይላል እንዲህ ነዉ!

<

© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved