የአገታ ቀበሌ ገ/ማህበር በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ ከሚገኙ ቀበሌዎች አንዷ ስትሆን መገኛዋ ፦
በሰሜን ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ
በደቡብ ስልጤ ወረዳ (አድበር ወለያ ቀበሌ)
በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ<
በስተ ምዕራብ ወሻኖ እና ጉግሶ ቀበሌዎች ያዋስኗታል
የአገታ ቀበሌ መልካዓ ምድራዊ አቀማመጥ በውሪብ እና በእንስላስ ታላላቅ ሰንሰለታማ ተራራዎች የታጠረች የገበቴ ቅርጽ የያዘች ፕላቶማ ገጽታ የላት ቀበሌ ናት።
የቀበለው የመሬት አቀማመጥ ለመሰረተ ልማት ምቹ ባለመሆኑ ማህበረሰቡ ለከፍተኛ ስቃይና እንግልት ተዳርጓል።
ተስፋ የተጣለባቸው ትውልዶች ያለ ውጤት ባክነዋል
ሴቶች ተደፍረዋል߹ህጻናት ጉልበታቸው በመንገድ ተበዝብዟል
ሴቶች ለአካላዊ እና ለስነ ልቦናዊ ጥቃቶች ተዳርገዋል
ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከመማር ይልቅ ወደ ከተማ ፈልሷል
የዋጋ ጥናቱን መሰረት በማድረግ እያንዳንዳቸው አራት የመማሪያ ክፍሎችን የሚይዙ 2ብሎኮችን ለመስራት በሚያስችል ሁኔታ በአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ የምህንድስና ክፍል ተጠንቶ ህዳር 2013 ግንባታ በይፋ ተጀመረ
ዲዛይን እና የዋጋ ጥናት በአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ኢንጅነሮች
ግንባታው እስኪጠናቀቅ በየ ሳምንቱ የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ኢንጂነሮች ከሙያ እገዛቸው በተጨማሪ በራሳቸው ወጪ እየተመላለሱ ከፍተኛ ወጭ በመቀነስ በጥራትና በፍጥነት እንዲሰራ የአንበሳውን ድርሻ ሸፍነዋል፡፡
ግንባታው ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ማቴሪያሎች ነው የተጠናቀቀው ለአብነት ያህል
ጣሪያውን ከፍተኛ ጥራት ባለው በኤጋሺት
ኮርኒሱን በጂፕሰም ቦርድ
ወለሉን ከፍተኛ ጥራት ባለው ሴራሚክ
የመማሪያ ጥቁር ሰሌዳወዎችን ከግድግዳው ከራሱ በኮንክሪት
የበሩን መግቢያ ኮለኖች ከፍተኛ ጥራት ባለው በክሊንከን
የመግቢያ ገላጭ ጽሁፍ መባይካ፡፡
በአሊቾ ው/ወረዳ በቡኔ ቀበሌ በተከሰተው እሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን የተደረገ ድጋፍ
30 ኩንታል ዱቄት
ሩዝ እና
26 የምግብ ዘይት
14 ጣቃ የተለያዩ አልባሳት
230 የቤት መስሪያ ቆርቆሮ
22 ፓኬት ሚስማር
በመለገስ ወገናዊ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡
የአገታ ኤጀሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል አረንጓዴ አሻራውን አኑሯል
100 ረጅሙ ፓይነስ ጽድ
40 አጭሩ ፓይነስ ጽድ
20 ዝግባ
20 ወይራ
40 ዘንባባ
10 ሸውሸዌ
10 ሩማን
20 ማንጎ
በድምሩ ከ260 በላይ ችግኞች ተተክለዋል
እቅዳችን ብዙ ነው
ተባብረን ከሰራን ከወረዳች እና ከዞናችን አልፎ ለመላው ሀገራችን የሚተርፉ መልካም ስራዎችን መስራት እንችላለን
© 2026/27 G.C የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፔጅ . All Rights Reserved የግንባታው ሂደት በከፊሉ በፎቶ ሲገለጽ
በግንባታ ሂደቱ ላይ የወረዳውና የህብረተሰቡ ተሳትፎ የላቀ ነበር ከተወሰኑት በፎቶ
በአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ የተሰራው ግንባታው አሁናዊ ገጽታ
የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ያከናወናቸው ተጨማሪ በጎ ተግባራት
የአገታ ኤጀሬ የላቶ ሀርዴ ያከናወናቸው ተጨማሪ በጎ ተግባራት ከተወሰኑት በፎቶ
አገታ ኤጀሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የችግኝ ተከላ
አገታ ኤጀሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የችግኝ ተከላ በፎቶ ሲገለጽ
በመጨረሻም
’’በባድ ዡቦ በሜልቾ ሬር ኢቀራን አኒርን’’ሀጂ አህመዲን ሀጂ ረዲ